ይድረስ ለጀዋር ሙሀመድ

From. WaltaTv.com
ይድረስ ለጀዋር መሀመድ

ባሻዬ ጀዋር ሆይ እንዴት አለህልኝ? ባክህ የኛን ነገር አትጠይቀን። አንተን አንሰማም ብለን ይህው የመከራ ፤ የስቃይ አይነት እየተፈራረቀብን ነው።
 
አንተ ግን እንዴት ነህ? ውይ ይቅርታ ለካስ አንተ በሰላም ልብህ አርፎ ትንቢቶችህ ሁሉ ሲፈፀሙ እያየህ ነው። የእውነት ገራሚ ሰው ነህ እኮ።
 
እስቲ በጥቂቱም ቢሆን አሁን ያለንበትን ሁኔታ አለፍ አለፍ ብዬ ልዘርዝርልህ። መጀመሪያ ግን በጣም ከሚያስቀው ነገር ልጀምርልህ ትንሽ ሳቅ።
 
ታስታውሳለህ አንዲት ሴትዮ እህተ ማሪያም የምትባለዋ ሴትዮ? አዎ እንደውም ጀዋር ይሞታል በቅርቡ ብላህ ነበር። አስታወስካት?
 
ይሄውልህ እሷ ሴትዮ እመቤቴ ማሪያም ተናግራኛለች ጌታ ነግሮኛል ብላ ብርሀኑ ነጋ ለዝች ሀገር ተስፋዋ እንደሆነ ፈጣሪ ልቡ በብርሀኑ እንዳረፈ ነገረችን።
 
ይሄን ጉድ ሰምተን ሳንጨርስ ሌላ ጉድ ደግሞ መጣልህ። የጴንጤ እህተ ማሪያም የሆነችው ሶፊ አወካት ሶፊያ ሽባባው? እሷ ደግሞ ሌላ ጉድ ይዛ መጣች።
 
ይሄውልህ የ ኦሮሚያ አምላክ ይመስገን ብላ ዘፈን አወጣች። ውይ ይቅርታ በጣም ከመቸኮሌ የተነሳ የኦሮሚያ አልኩኝ የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ብላ ነው።
 
መቼም አንተ የለህም ብለው ሀገሪቱን የውርጋጥ መጫወቻ አደረጓት እኮ። አሁን ደግሞ በደንብ እንዲገባህ ቆይ ለምን በእንግሊዘኛ አልነግርህም?
 
Addis Ababa Love Dr.Abiy Ethiopia is # Jeorge Floyd. Message for American. ጄዌ ሆይ? ያወራውህ ገባህ አይደል?
 
ይህው ይሄ ትላንትና መስቀል አደባባይ ወያኔን ለማውገዝ የተጠራ ሰልፍ ላይ ብዙ የተማሩ ሰዎች ተገኝተው ነበር እና የነሱ መልክት ነው።
 
እንግሊዘኛው ላይገባህ ይችላል ቆይ ልተርጉምልህ። የአዲስ አበባ ፍቅር ዶ / ር አብይ # ጆርጅ ፍሎይድ ናት ፡፡ መልእክት ለአሜሪካዊ።
 
በቃ እንዲህ ነው ትርጉሙ። ይህው አንተን አስረው ሀገሪቱን የውርጋጥ መጫወቻ አደረጓት እኮ የሚገርምህ ይሄን ሁሉ ህዝቡ እያየ ደንዝዞልሀል።
 
ሌላው ስለ ጦርነቱ ምን ብዬ ልንገርህ? መከላከያ በገፍ ተማርኮ ትግራይ ውስጥ ቁጭ ብሎ በነፃ እየትቀለበልህ ነው። መንግስት የኔ አይደሉም ብሎ ክዷል።
 
እረ እንደውም ባጫ ደበሌን አወከው? አዎ እሱ ሰውዬ ይሄ ሁሉ ምርኮኛ ሲመለከት ነገሩ በጣም ከአእምሮ በላይ ሲሆንበት ታላቁ ሩጫ ነው ብሎ እርፍ።
 
ደግሞ እረስቼው ብርሀኑ ጁላን አስታወስከው? ለነገሩ አሁን ብታየው አታውቀው። ታግቶ ነው ያለው። የሀረር ሰንጋ የመሰለው ሰውዬ አሁን ታሟል።
 
ብቻ ምን አለፋህ ህዝቡ ግራ ተጋብቷል መንቃት አልቻለም። ንቃ ብለህ ስትመክረው በጣም ብዙ ከመደደቡ የተነሳ አይሰማህም።
 
ይቅርታ ጀዋርዬ አረዘምኩብህ አይደል? ለማንኛውም በቃ ልጨርስ ከዛ በፊት ግን አንድ ነገር ሹክ ልበልህ ስለ ኦሮሚያ ምንም እንዳታስብ።
 
አንተ የጮክለት ህዝብ አሁን ተረጋግቶ በጥቂቱም ቢሆን አንፃራዊ ሰላም አለው። ልማቱ በደንብ እየተፋጠነ ነው። ኦነግ እራሱ ልማት ጀምሯል።
 
ሌላው ስለ አብይ ምንም ያልነገርኩህ ያው አብይ እስከ መስከረም ድረስ እንጂ ከመስከረም በኋላ አይቀጥልም ይባላ። እኔ ግን አይመስለኝም።
 
ወይኔ እረስቼው ስለ ሶፊያ አንድ ነገር ልጨምርልህ እማ ምን ብላ መሰለህ የዘፈነችው? እልል በይ ሀገሬ እልልበይ ኢትዮጵያ እልል በይ።
 
ካለች በኋላ የታሰሩ ተፈቱ ፤ ያለቀሱ ፤ ሳቁ ፤ ያዘኑ ተፅናኑ ምናምን ብላ አፀፍንም መሰለህ? ቆይ ያንተ መታሰር እንኳን ምንም አልመሰላትም። አይገርምም?
 
ደግሞ በዚህ ቂም እንዳትይዝባት እኔ ያው ከሰው የሰማሁት ነው ከዶ/ር ወዳጄ ነህ ጋር ከተፋታች በኋላ ጤናዋ እንደድሮ አይደለም ይባላል።
 
ብቻ ለዛም መሰለኝ የውስጥ ጩህቷን ለመደበቅ አደባባይ ላይ እሪ በይ ሀገሪ እሪ በይ ኢትዮጵያ የሚል ዘፈን ያወጣቸው እሪ ማለት ፈልጋ መስለኝ።
 
እኔ የምልህ ጋሽ በቄ ግን እንዴት ናቸው? ታውቃለህ ጋሽ በቄ እኮ ማለት የእውነት ቂም የማያውቁ ሰው ናቸው ሰላም በልልኝ ቻዎ ጀዌ።

Published by ወያናይ ትግራዋይ ጀግንነት - WOYANAY HEROISM TIGRAY TPLF

WELCOME TO WEBSITE ወያናይ ትግራዊያን ጀግንነት-WOYANAY HEROISM TIGRAY TPLF VOICE OF THE TIGRAYANS WEBSITES HOME PAGE We will discuss various realities of the people of Tigray as well as the heroism of Tigray and the positive issues we need to support for our government in Tigray.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

Create your website with WordPress.com
Get started
%d bloggers like this: